Loading...
Image

አቶ ሐብታሙ ደረጀ

የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ

የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር

የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት የክፍለ ከተማውን የሰላምና የጸጥታ አስተዳደር ጉዳዮች የማስተዳደር እና ህዝቡን የሰላም ባለቤት የማድረግ ሃላፊነቶች ተቀብሎ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እንዲሁም ምልዓተ ህዝቡን በማሳተፍ በርካታ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ጽ/ቤቱ በአዋጅ የተሰጡትን ተግባርና ኃላፊነቶች ከሌሎች ህግ አስከባሪ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በክፍለ ከተማችን ውስጥ በተለያዩ ጊዜያትና አጋጣሚዎችን በመጠቀም ለመፈጸም ታቅደው የነበሩ የስርዓት አልበኝነት፤ የወንጀል፤ የሁከትና ብጥብጥ እና የሽብር ተግባራት እንዳይሳኩ ከማድረግ በተጨማሪ የሚከበሩ ሃይማኖታዊና ባህላዊ የአደባባይ ክብረ በዓላት ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከናወኑ በማድረግ የህግ የበላይነት ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ የክፍለ ከተማችን የሰላም የጸጥታና የህግ ማስከበር ስራዎች በተቋም አቅም መፈጸም የሚያስችል አሰራር ለመፍጠር እየተደረጉ የሚገኙ ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎች እንደተጠበቁ ሆነው የክፍለ ከተማችን ሰላምና ጸጥታ ለማስተዳደር ሃላፊነት የተሰጣቸው በየደረጃው የሚገኙ በሰው ሃይል ፤በግብዓት፤ በአሰራር እና በአደረጃጀት በማጠናከር ተልዕኮውን በተገቢው የሚፈጽም የህግ አስከባሪ ተቋም እንዲሆኑ ማድረግ ጊዜው የሚጠይቀው ሃላፊነት እንደ መሆኑ መጠን የክፍለ ከተማችንን ሰላምና ጸጥታ ለማረጋገጥ መላው የክፍለ ከተማችን ህዝብ እና ተቋማት በተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ማሳተፍ ከሚቻልባቸው ዘዴዎች መካከል ድህረ-ገጽ አንዱ እንደ መሆን መጠን የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ድህረ-ገጽ በመጠቀም ሰላም፤ ጸጥታ እና ህግ ማስከበርን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊ በመሆን የዜግነት ሃላፊነታችሁን እንድትወጡ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ::አመሰግናለሁ! አቶ ሃብታሙ ደረጀ የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ

180,605

ወንዶች

196,427

ሴቶች

377,032

ጠቅላላ ነዋሪዎች

አስተባባሪዎች

ጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት

Image

ፍቅሩ ጠና

ሰላም እሴት ግንባታ አደ/ና/ተ/ድ/ክ/ስ/አስተዳደር

Image

አሸናፊ ጌታቸው

የፀጥታ ጉዳዮች ክትትልና ቁጥጥር ኦፕሬሽን ስራዎች አስተባባሪ

Image

ደበላ ተሾመ

የፀጥታ መረጃ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ፈጣን ምላሽ ስራዎች አስተባባሪ

Image

ኮ/ር በየነ ገቢሳ

የህዝብ አደረጃጀት ተሳትፎና ብዙሃን ማህበራት ድጋፍ ስራ አስተባባሪ

የቡድን መሪዎች

ጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት

Image

አምሳሉ ደረሰ ቤሮ

የሰላም እሴትና የሀይማኖት ጉዳዮች ቡድን መሪ

Image

ዳምጠው አያሌው

የፀጥታ ጉዳዮች ክትትልና ቁጥጥር ኦፕሬሽን ቡድን መሪ

Image

ታደሰ ረታ

የህዝብ አደረጃጀት ተሳትፎና ብዙሃን ማህበራት ድጋፍ ክትትል ቡድን መሪ

Image

ምንአወጋሁ ነጋሲ

የፀጥታ መረጃ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ፈጣን ምላሽ ቡድን መሪ

በክፍለ ከተማው ውስጥ የተከናወኑ ክንውኖች

ዜናዎች

የጉለሌ ክፍለ ከተማ

አስተዳደር

በ 2022 አዲስ አበባ ከተማ በህዝብ ተሳትፎና ባለቤትነት ሰላምና ጸጥታ የሰፈነባት፤ የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት፣ ለኑሮ ለስራ እና ለመዝናኛ ተመራጭ የሆነች ከተማ ሆና ማየት

የተቀናጀ የጸጥታ ጉዳዮች አስተዳደር እና የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያና ፈጣን ምላሽ ስርዓትን ተግባራዊ በማድረግ ወንጀልን በመከላከል፤ የሰላም እሴቶችን በመገንባት፣ በሃይማኖትና እምነት ተከታዮች መካከል መከባበርና መቻቻል እንዲሰፍን በማድረግ፤ የክትትል፤ ቁጥጥር እና ቀልጣፋ አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት በመዘርጋት፣ ነዋሪውንና ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎና ባለቤትነት በማረጋገጥ ሰላም፣ ጸጥታና ደህንነቷ የተጠበቀ እና ህግና ስርዓት የተከበረባት ከተማ ማድረግ ነው፡

- የህግ የበላይነትን ማክበርና ማስከበር
- ለላቀ ሰላምና ጸጥታ መትጋት
- ታማኝነትና ተጠያቂነት
- ተቋማዊ አጋርነት
- ፍትሐዊነትና ሰብዓዊነት
- ሚስጥር ጠባቂነት
Image

Get Our App

image description