Loading...

ስለ እኛ

Image

አቶ ተስፋዬ ፈይሳ

የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር

የክፍለ ከተማው ኃላፊ መልዕክት

የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት የክፍለ ከተማውን የሰላምና የጸጥታ አስተዳደር ጉዳዮች የማስተዳደር እና ህዝቡን የሰላም ባለቤት የማድረግ ሃላፊነቶች ተቀብሎ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እንዲሁም ምልዓተ ህዝቡን በማሳተፍ በርካታ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ጽ/ቤቱ በአዋጅ የተሰጡትን ተግባርና ኃላፊነቶች ከሌሎች ህግ አስከባሪ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በክፍለ ከተማችን ውስጥ በተለያዩ ጊዜያትና አጋጣሚዎችን በመጠቀም ለመፈጸም ታቅደው የነበሩ የስርዓት አልበኝነት፤ የወንጀል፤ የሁከትና ብጥብጥ እና የሽብር ተግባራት እንዳይሳኩ ከማድረግ በተጨማሪ የሚከበሩ ሃይማኖታዊና ባህላዊ የአደባባይ ክብረ በዓላት ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከናወኑ በማድረግ የህግ የበላይነት ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ የክፍለ ከተማችን የሰላም የጸጥታና የህግ ማስከበር ስራዎች በተቋም አቅም መፈጸም የሚያስችል አሰራር ለመፍጠር እየተደረጉ የሚገኙ ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎች እንደተጠበቁ ሆነው የክፍለ ከተማችን ሰላምና ጸጥታ ለማስተዳደር ሃላፊነት የተሰጣቸው በየደረጃው የሚገኙ በሰው ሃይል ፤በግብዓት፤ በአሰራር እና በአደረጃጀት በማጠናከር ተልዕኮውን በተገቢው የሚፈጽም የህግ አስከባሪ ተቋም እንዲሆኑ ማድረግ ጊዜው የሚጠይቀው ሃላፊነት እንደ መሆኑ መጠን የክፍለ ከተማችንን ሰላምና ጸጥታ ለማረጋገጥ መላው የክፍለ ከተማችን ህዝብ እና ተቋማት በተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ማሳተፍ ከሚቻልባቸው ዘዴዎች መካከል ድህረ-ገጽ አንዱ እንደ መሆን መጠን የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ድህረ-ገጽ በመጠቀም ሰላም፤ ጸጥታ እና ህግ ማስከበርን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊ በመሆን የዜግነት ሃላፊነታችሁን እንድትወጡ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ::አመሰግናለሁ! አቶ ተስፋዬ ፈይሳ የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ

በሰላም መጣችሁ

አስተባባሪዎች

ጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት

Image

ፍቅሩ ጠና

ሰላም እሴት ግንባታ አደ/ና/ተ/ድ/ክ/ስ/አስተዳደር

Image

አሸናፊ ጌታቸው

የፀጥታ ጉዳዮች ክትትልና ቁጥጥር ኦፕሬሽን ስራዎች አስተባባሪ

Image

ደበላ ተሾመ

የፀጥታ መረጃ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ፈጣን ምላሽ ስራዎች አስተባባሪ

Image

ኮ/ር በየነ ገቢሳ

የህዝብ አደረጃጀት ተሳትፎና ብዙሃን ማህበራት ድጋፍ ስራ አስተባባሪ