#ጳጉሜ_1_የጽናት_ቀን
ትውልዱ በሃገራዊ ጥቅም ላይ ባለመደራደር ጽኑና ሃያል የሆነች ኢትዮጵያን መገንባት እንደሚገባ ተገለጸ።
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ጳጉሜን አንድ የጽናት ቀን "ፅኑ መሠረት ብርቱ ሀገር" በሚል መሪ ቃል በፓናል ውይይት አካሄደ።
በፓናል ውይይቱ ላይ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እንደተናገሩትን ሃገራችን ኢትዮጵያ በበርካታ ፈተናዎችን በማለፍ በጽናት ያከናወናቸው የአረንጓዴ አሻራ ተግባራችን ፣ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድባችን ፣ የኮሪደር ልማትና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክቶቻችን እንደ ሀገር ያለንን አይበገሬነት እና በፈተና ሳንበገር ወደ ፊት መጓዝ ስለ መቻላችን ማሳያ ነው ብለዋል።
ዋና ስራ አስፈጻሚው አክለውም የጽናት ቀንም ፈተናዎችን በፅናት በማለፍ ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማስመዝገብ እየተደረጉ የሚገኙ ብርቱ ጥረቶችን በመዘከር ለአዳዲስ ተልዕኮዎች እና ለላቁ ድሎች የምንዘጋጅበት ነው ብለዋል፡፡
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ደረጀ የሀገር ወዳድነት ፣ የፅናትና የአርበኝነት ምንነቶችን በሰፊው የሚዳስስ የማወያያ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን የጸጥታና የደኅንነት ተቋማትን ከማዘመን ጀምሮ እስከ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ እውን መሆን ድረስ ያገኘነው ታላቅ ስኬት፤ የአንድነታችን፣ የጋራ ዓላማችን እና ያላሰለሰ ጽናታችን ውጤት መሆኑን በኩራት እናረጋግጣለን ለእነዚህ ስኬቶች መንገድ የከፈቱት ጀግኖቻንን ድፍረት፣ የመስዋዕትነትና የማይናወጥ ጽናትን እናስታውሳለን፤ እናከብራለንም ብለዋል።
የዛሬው ዕለት ፈተናዎችን ሁሉ ወደ መልካም አጋጣሚ ቀይረን ኢትዮጵያን ወደ አዲስ የብልጽግና፣ የክብርና የዘላቂ ከፍታ ለማድረስ ቃል የምንገባበት ነው ሲሉም ገልጸዋል።
በአዲስ ተስፋ፤ በጽኑ መንፈስና በማይናወጥ አንድነት መቆም እንደሚገባ አስረድተው፤ ኢትዮጵያ ወደ ብልጽግናና ታላቅነት የምታደርገውን ጉዞ በይበልጥ ከፍ የምታደርግበት አዲስ ምዕራፍ መጀመሩንም ገልጸዋል።
በፓናል ውይይት ላይ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች የፌደራልና የከተማ ፖሊስ አባላት ፣ የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች ፣ የሃይማኖት አባቶች ፣ የሰላም ሰራዊት አባላት እንዲሁም ሴቶችና ወጣቶች ተሳትፈዋል ።