የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት በመሠረታዊ የስራ ሂደት ክለሳ ጥናት ለተዘጋጁ የስራ መደቦች የሰራተኞች የድልድል አፈፃፀም መመሪያ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
ጽ/ቤቱ ለክፍለ ከተማና ለወረዳ የሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ሰራተኞች በመሠረታዊ የስራ ሂደት ክለሳ ጥናት ለተዘጋጁ የስራ መደቦች የሰራተኞች የድልድል አፈፃፀም መመሪያ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል ።
በመድረኩ ላይ ሪፎርሙ ግልፀኝነት ፣ ፍትሐዊነትና ተጠያቂነትን ታሳቢ ያደረገ ሆኖ በተለይም ከብሔር ከሀይማኖትና መሰል ተጓዳኝ ነጥቦች የፀዳ ሆኖ ድልድሉ የሚፈፀም መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ሰራተኛው እንዲሁም ቡድን መሪዎች በሚፈፀመው ሪፎርም ላይ በመመሪያው መሠረት ሊያሟሏቸው የሚገቡ መብትና ግዴታዎችን ማክበር እንደሚገባ የተጠቀሰ ሲሆን በተለይም ሪፎርሙ ሲሰራ ልንቀነስ ነው የሚል ያልተገባ አልቧልታና ውዥንብር ውስጥ ከመግባት ተቆጥቦ ህግና መመሪያው በሚያዘው መሠረት ተወዳድረው በመመደብ የተጣለባቸውን ሃላፊነት መወጣት እንዳለባቸው ተገልጿል።
በስልጠና መድረኩ ላይ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ደረጀ እንደገለፁት በደንብ ቁጥር አዋጅ 156/2016 አማካኝነት ሰራተኛው በተረጋጋና በልምድ በካበተበት መልኩ ውጤታማ ይሆን ዘንድ ለሪፎርሙ ልዩ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ገልፀዋል ።
ኃላፊው አክለውም ሰራተኛው ሲደለደልም ግልፀኝነትና ፍትሐዊነትን የተላበሰ ሆኖ ብልሹ አሰራርንና የስነ ምግባር ጉድለትን በማረም የመንግስትን አገልግሎት ውጤታማ ለማድረግ የተገልጋዩን እርካታ ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑን ሁሉም ሰራተኛና ቡድን መሪዎች ሊገነዘቡ እንደሚገባም ገልጸዋል።