Loading...

ዝርዝር ዜና

የሁሉንም ህብረተሰብ የሰላም ባለቤትነት ተሳትፎውን በማሳደግ የክፍለ ከተማው ሰላምና ጸጥታ በማረጋገጥ ውጤታማ ስራ መሰራቱ ተገለፀ።

user 30-Aug-2026 ፀጥታ

የጉለሌ  ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት 8ኛ ዙር የማካካሻ ኮርስ እጩ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላትን አስመረቀ።

(ጉለሌ ኮሙኒኬሽን ፣ 14 -12 -2018 ዓ.ም)
የክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት በ8ኛ ዙር የማካካሻ ኮርስ ለ1000 እጩ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላትን የንድፈ ሃሳብና የተግባር ስልጠና በመስጠት አስመርቋል።

በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እንደተናገሩት የሰላም ሰራዊት አባላት የከተማችንን ሰላምና ጸጥታ ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በመሆን ሀገራዊና ከተማዊና ሃይማኖታዊ የአደባባይ ክንውኖች በሰላም እንዲከናወኑ ትልቅ ድርሻ ተወጥታችኋል ያሉ ሲሆን አዲስ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላት ያገኛችሁትን ስልጠና በተግባር በማዋል የድርሻችሁን ማበርከት ይገባችኋል ብለዋል፡፡

ዋና ስራ አስፈጻሚው አክለውም የሰላም ሰራዊቱ የሰላም አምባሰደርነቱን በተግባር እያረጋገጠ ከውስጥ ከውጪ የሚነሱ ግጭቶችን በመመከት በዛሬው ዕለት የተመረቃችሁ አዲስ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላት የአካባቢያችሁን እንዲሁም ክፍለ ከተማችሁን ሰላም ጸጥታ ከጸረ ሰላም ሃይሎች በመጠበቅ የተሰጣችሁን ኃላፊነት በተግባር መወጣት አለባችሁ ብለዋል፡፡

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ  አቶ ተስፋዬ ፈይሳ  በበኩላቸው የሰላም ሰራዊት አባላት የወሰዱትን የንድፈ ሀሳብና የተግባር ስልጠና ወደ ተጨባጭ ውጤት በመቀየር የአካባቢያቸውንና የከተማዋን ሰላም በተጠናከረ መልኩ ማስቀጠል እንዳለባቸው አብራርተዋል።

​የስልጠናው ተሳታፊ አዲስ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላት በበኩላቸው፣ ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ለአካባቢያቸው ሰላም መስፈን ዘብ በመቆም ወንጀልን ለመከላከል ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።