Loading...

ዝርዝር ዜና

የጉለሌ ክፍለ ከተማ የጸጥታ የጋራ ግብረ ሃይል ክፍለ ከተማውን ሰላምና ጸጥታ ለማስጠበቅ በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ ገለጸ።

user 11-Jul-2025 ፀጥታ

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር የጸጥታ ጥምር ሃይል  በተሰሩ የሰላምና ጸጥታ ማስጠበቅ ስራዎችና በቀጣይ የክፍለ ከተማውን የጸጥታ ሁኔታ በተጠናከረ አሰራር ማስጠበቅ በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ ውይይት አድርጓል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ  እንደተናገሩት የጸጥታ ጥምር ሃይሉ ክፍለ ከተማውን ሰላማዊ  ለማድረግ ቅንጅታዊ ስራዎችን ለቀጣይ አጠናክሮ በመሰራትና የነበሩ ክፍተቶችን በማረምና በማስተካከል የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ በትኩረት መንቀሳቀስ ይገባል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ምክትል  ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር በበኩላቸው በከተማዋ ሰላምና ጸጥታ ስርዓቱን የማስጠበቅ  ለማድረግ የጸጥታ መዋቅሩ ከሰላም ሰራዊቱ ጋር በመናበብ የስምሪትና የመረጃ ልውውጥ  ስርዓታችንን በማስተካከል ህብረተሰቡ ሰላሙን ከጸረ ሰላም ሃይሎች እንዲጠብቅ በማድረግ ይገባል ብለዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ደረጀ በበኩላቸው በክፍለ ከተማ ደረጃ  በተሰራው የተቀናጀ ስራ በርካታ ውጤቶች መመዝገባቸውንና ለጸጥታ ስጋት የተባሉትን ነገሮች ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል ከአጎራባች የኦሮሚያ ከተሞች ጋር በመቀናጀት ፍተሻና አሰሳ ስራዎች ተጠናክረው በመሰራት ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

በቀጣይ የፀጥታ ኮማንድ ፖስቱ የሰላም ሰራዊቱን  ማጠናከር፣ ስጋት ያለባቸው ቦታዎችን የተለየ በቅንጅት በመስራት ክፍለ ከተማውን ሰላማዊ ማድረግ  እንደሚገባ ተገልጿል።