በቀን በቀን 11 -07 -2017 ዓ.ምወቅቱን የጠበቀ ስልጠና በመስጠት የሰላም እሴት ግንባታ ስራዎች አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ለወረዳና ለክፍለ ከተማ ባለሙያዎችና አመራሮች ( Citizen Engagement Mobile Application ) እና በተቋሙ ግብ ተልዕኮ ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ደረጀ እንደተናገሩት ስልጠናው ለአመራሮች ለአስተባባሪዎችና ለቡድን መሪዎችና ሁሉም ባለሙያ ተመሳሳይ ግንዛቤ እውቀትና ክህሎት ይዞ የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ ለማስቻል እንደሆነ ተናግረዋል።