Loading...

ዝርዝር ዜና

የጉለሌ ክፍለ ከተማ የገበያ ማረጋጋት፣ የህገ ወጥ ንግድ ቁጥጥርና ግብረ ሃይል የ90 ቀናት ዕቅድ ከተጀመረ ጀምሮ የተከናወኑ ተግባራትን ውይይት አድርጓል።

user 17-Jul-2025 ፀጥታ

በውይይቱ በአቅርቦትና እና ቁጥጥር በሚሰሩ ስራዎች ላይ ትኩረት አደረገ ሲሆን በቀጣይ በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ሰፊ ውይይትም ተደርጓል። 

የውይይት መድረኩን የመሩት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ  አቶ ሀብታሙ ደረጀ እንደተናገሩት የክ/ከተማው ገበያን ለማረጋጋትና የኑሮ ውድነትን ለመከላከል የተሻለ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱ አንስተው በ90 ቀናት ግብረ ሀይሉ ዕቅዱን ለማሳካት የምርት አቅርቦት እና የንግድ ቁጥጥሩን አጠናክሮ በማስቀጠል የግብይት ስርዓቱን የማስተካከል እና ለሸማች ማህበረሰብ  ፍትሃዊ ተደራሽነት እንዲኖር በማድረግ የህግ የበላይነትን እያረጋገጡ መሄድ እንደሚገባ ገልጸዋል። 

ገበያን ለማረጋጋትና የኑሮ ውድነትን ለመቅረፍ አቅርቦት ማሻሻል፣ ቅዳሜና እሁድ ገበያ ስታንዳርድ ማስጠበቅና ተደራሽነት ማስፋፋት፣ የሌማት ቱሩፋት ምርት ወደ ገበያ ማስወጣት፣ የአምራች ኢንዱስትሪዎች መደገፍ፣  ስራ በትኩረት መስራት እንዳአለባቸው ገልፀዋል።

 ህገ ወጥ ንግድና ኮንትሮባንድ እንዲሁም የምሽት ንግድ ቁጥጥርን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል።

በመድረኩ የቀጣይ 90 ቀናት ዕቅድ በክፍለ ከተማው ውይይት የተካሄደ ሲሆን የክ/ከተማና የወረዳ ግብረ ሀይል አባላት  ዕቅዱን ለማሳካት የራሳቸውን ሚና እንደሚወጡ እና ውጤታማ ስራ በቅንጅት እንደሚሰሩ ገልፀዋል።