Loading...

ዝርዝር ዜና

የመከባበርና የአብሮነት ባህልን በማጠናከር ለሰላም እሴት ግንባታ የድርሻቸውን ማበርከት እንዳለባቸው ተገለጸ።

user 03-Jun-2025 ፀጥታ

የመከባበርና የአብሮነት ባህልን በማጠናከር ለሰላም እሴት ግንባታ የድርሻቸውን ማበርከት እንዳለባቸው ተገለጸ።

(ጉለሌ ኮሙኒኬሽን ፣ 25 -09-2017 ዓ.ም )

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት  ለተለያዩ የሰላም አደረጃጀቶች በሰላም አስፈላጊነት  እሴት ግንባታ ዙሪያ  ውይይት አድርጓል።

በመድረኩም  በአብሮነትና መከባበር ፣ ስለ ሰላም ምንነት ፣ የሰላም እጦት መንስኤዎች፣ የሰላምና የአብሮነት እጦት ችግሮች እና የሰላም አደረጃጀቶች  በሰላም ግንባታ ያላቸው ሚና ዙሪያ ገለጻ ተደርጓል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ  ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ደረጀ  እንደተናገሩት የህብረተሰባችን ትልቅ ሃይል የያዘ በመሆኑ  ለአካባቢው ሰላም መጠበቅና  የሰላም እሴት ግንባታ ላይ ያላቸው ሚና ትልቅ መሆኑን ተናግረው ለዘመናት  የህብረተሰቡን አብሮነትና መከባበር ላይ ያለውን ሚና በሚያጠናክሩ ነገሮች ዙሪያ በስፋት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ የሰላም እሴት ግንባታ ስራዎች አስተባባሪ አቶ ፍቅሩ ጠና በበኩላቸው  የሰላም አደረጃጀቶች  ከመንግስት ጋር  የጋራ በሚያደርጉ በልማትና የጸጥታ ስራዎች ዙሪያ በቅንጅት በመስራት ለሀገር አንድነት አስተዋጽዖ ማበርከት ይገባል ብለዋል