Loading...

ዝርዝር ዜና

ክፍለ ከተማው አስተዳደር በ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ለማስፈጸም በተዘጋጀ እቅድ ላይ የፈተና ግብረ ሀይል በዛሬው እለት ውይይት አካሔዷል።

user 30-Jun-2025 ፀጥታ

የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ2017 ዓም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና በሰላም እንዲጠናቀቅ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ተሳተፎና ርብርብ እንደሚጠይቅ ተገለጸ።

(ጉለሌ ኮሙኒኬሽን ፣ 16 - 10 - 2017 ዓ.ም)

በክፍለ ከተማው አስተዳደር በ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ለማስፈጸም በተዘጋጀ እቅድ ላይ የፈተና ግብረ ሀይል በዛሬው እለት ውይይት አካሔዷል።

አስተዳደሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ከክፍለ ከተማና ከወረዳ አመራሮች እንዲሁም ከተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ደረጀ እንደተናገሩት የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በክፍለ ከተማው ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ የጸጥታ መዋቅሩ ከዚህ በፊት የተሰጡትን ፈተናዎች ያጋጠሙ ሁኔታዎችን ልምድ በመውሰድ የቅድመ ዝግጅቱን ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል ብለዋል።

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና በክፍለ ከተማው በስኬት እንዲጠናቀቅ የቅንጅት ስራችንን በማጠናከር ለፈተናው እንቅፋት የሆኑ ተግባራትን በመከላከል ስኬታማ የፈተና አሰጣጥ እንዲሆን መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ኮራ በበኩላቸው ጽ/ቤቱ 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጸው የሙከራ ፈተናዎችን በተለያዩ መፈተኛ ጣቢያዎች እየሰጠ ነው ተግባሩም ዕለት በዕለት እየተገመገመ የሚያጋጥሙ ችግሮችም እየተቀረፉ ይገኛል ያሉ ሲሆን ፈተናው ተሰጥቶ እስከሚጠናቀቅ ቅንጅታችንን አጠናክረን ማስቀጠል አለብን ብለዋል።

የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አራጌ እሸቴ በበኩላቸው በሁሉም የፈተና መስጪያ ጣቢያዎች ፈተናው ሊያውኩ የሚችሉ ጉዳዮችን በመለየት የተጠናከረ የፀጥታ ስራ ለመስራት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሰራቱን አብራርተዋል።

የሚሰጠው ፈተና ከወረቀት ወደ ኦልላይን የፈተና ስርዓት መግባቱ ከዚህ ቀደም ሲነሱ የነበሩ ችግሮችን ሊቀርፍ እንደሚችልም አስገንዝበው የፀጥታ ስራ ቅድሚያ የሚሰጠው እንደሆነም ተናግረዋል።

የ2017 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ሰርተፊኬት ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሀምሌ 08 ድረስ ይሰጣል።