በቀን በቀን 21 -08 -2017 ዓ.ምየሰላም ሰራዊቱን አቅም ለመገንባት የንድፈ ሃሳብና የተግባር ስልጠና በመስጠት የሰላም አምባሳደርነቱን ሚና መወጣት እንዳለበት ተገለጸ።
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት የ4ኛ ዙር ኮርስ ለሰላም ሰራዊቱ ሰልጣኞች እየተሰጠ የሚገኘው የአቅም ግንባታ በመስክ ስልጠና እንደቀጠለ ነው።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት የተወጣጡ የሰላም ሰራዊት አመራር አባላት የመስክ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ደረጀ እንደገለጹት የሰላም ሰራዊቱ የአካባቢው የሰላም ዘብ እንዲሆን በ4ኛው ዙር አዳዲስ ለተመለመሉ የሰላም ሰራዊት አባላት የንድፈ ሃሳብ እና የተግባር ስልጠና እየሰጠ ይገኛል ብለዋል።
ስልጠናው የሰላም ሰራዊቱ ለጸጥታ መዋቅሩ አጋዥ ሃይል መሆናቸው አጠናክሮ እንዲቀጥሉ በማስቻል የክፍለ ከተማው ሰላምና ጸጥታ ዋና ተዋናይ እንዲሆኑ ለማድረግ ያለመ ነው ብለዋል።