Loading...

ዝርዝር ዜና

ህብረተሰቡ የክፍለ ከተማውን ሰላምና ጸጥታ መጠበቅ የድርሻቸውን ማበርከት እንዳለበት ተገለጸ።

user 11-Jul-2025 ፀጥታ

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት  የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸሙን  ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል።

(ጉለሌ ኮሙኒኬሽን ፣  03 - 11 - 2017 ዓ.ም)

ጽ/ቤቱ በበጀት ዓመቱ ዕቅድ አፈጻጸሙን ህብረተሰቡ የሰላም ባለቤት እንዲሆን የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በመስራት ህብረተሰቡ ከሰላም ሰራዊቱና ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በመሆን የአካባቢውን ሰላም እንዲጠብቅ የተሰራበት ህዝባዊና ሃይማኖታዊ በዓላት ያለምንም የጸጥታ ችግር መከበር መቻላቸውን በሪፖርቱ ተብራርቷል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ደረጀ እንደተናገሩት  በክፍለ ከተማው ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመስራት የህብረተሰቡን ሰላምና ጸጥታ ማስጠበቅ ተችሏል ያሉ ሲሆን  ከህብረተሰቡ የሚነሱ ቅሬታዎች እንዲሁም ህገ ወጥነትን በመከላከል ከጸጥታ አካላት ጋር ያላቸው ጥምረት በማጠናከር ወንጀሎችን ለመቆጣጠር በትኩረት መስራት ይገባችኋል ብለዋል።

ኃላፊው አክለውም ከፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅተው ሚናቸውን እንዲወጡ ፣በሰላም እሴት ግንባታ ላይ የሰላምን ምንነትና አስፈላጊነት በአግባቡ ተረድተው  ለማህበረሰቡ ሠላም ተግተው እንዲሰሩ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።