Loading...

ዝርዝር ዜና

ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠንከር የክፍለ ከተማውን ሰላምና ጸጥታ ማስጠበቅ እንደሚገባ ተገለጸ።

user 08-Jul-2025 ፀጥታ

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በተከናወኑ ስራዎች  ከተለያዩ 18 ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅታዊ አሰራር ዙሪያ ውይይት አካሄዷል።

በውይይቱ ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ  አቶ ሀብታሙ ደረጀ እንደተናገሩት በክፍለ ከተማው በተከናወኑ የቅንጅት ስራዎች ሰላምና ጸጥታን ማምጣት መቻሉን የገለጹ ሲሆን ወቅቱ የክረምት ወራት ወንጀሎች የሚበዙበት በመሆኑ ከዚህ በፊት በተጠናከረ መልኩ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

 ህብረተሰቡ ላይ የኑሮ ውድነቱ የሚያደርሰውን ጫና ለመከላከል በቅንጅት በግብረ ሃይል ህገ ወጦችን ወደ ህጋዊ መንገድ እንዲገቡ እንዲሁም በተለያዩ ዘርፎች ተሰርቷል በቀጣይም አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።

በውይይቱ ላይ ከደንብ ማስከበር ፣ ከመንገድ ትራንስፖርት ፣ ከትራፊክ ማኔጅመንት ፣ ከንግድ  እንዲሁም ሌሎች 18 ባለ ድርሻ አካላት ተሳትፈውበታል።