Loading...

ዝርዝር ዜና

.በጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመትከኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ መነ አብቹ እና ኤጀርሳ ጎሮ ጋር ባለፉት ስምንት ወራት በቅንጅት የተሰሩ የሰላምና ጸጥታ ስራዎችና በቀጣይ በሚከተናወኑ ተግባራት ዙሪያ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የተደረገ ውይይት

user 13-Jun-2025 ልማት

በቀን በቀን 13 -07 -2017 ዓ.ምየጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት በባለፉት 8 ወራት ከአጎራባች ኦሮሚያ ሸገር ከተሞች የመነ አብቹ እና ኤጀርሳ ጎሮ ጋር በቅንጅት በተከናወኑ ተግባራት የህብረተሰቡን ሰላምና ጸጥታ ማስጠበቅ መቻሉን ተገለጸ።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ከኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ መነ አብቹ እና ኤጀርሳ ጎሮ ጋር ባለፉት ስምንት ወራት በቅንጅት የተሰሩ የሰላምና ጸጥታ ስራዎችና በቀጣይ በሚከተናወኑ ተግባራት ዙሪያ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ።

ጽ/ቤቱ በባለፉት 8 ወራት ከአጎራባች የሸገር ከተሞች ጋር በጋራ በመሆን ህገ ወጥነትን በመከላከል ፣ በሰላም ጉዳይ የህዝብ ለህዝብ ትስስር በመፍጠር ፣ ጠንካራ የመረጃ ቅብብሎሽ ስርዓት በመፍጠር የተለያዩ የጽንፈኛ ሃይሎች እንቅስቃሴ በማክሸፍ ፣ የጸጥታ የጋራ ግብረ ሃይል የህግ ማስከበር ስራዎች ፣ የፍተሻና የአሰሳ ስራዎች በማከናወን ሃይማኖታዊና የአደባባይ በዓላትና የተለያዩ ሁነቶችን ያለምንም የጸጥታ ችግር ማክበር መቻሉን ተገልጿል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ደረጀ እንደተናገሩት በባለፉት 8 ወራት በቅንጅት በትብብር በመስራት በተከናወኑ ተግባራት በወንጀል ቅነሳ ፣ የጽንፈኛ ሃይሎች እንቅስቃሴ ቀንሷል ያሉ ሲሆን በቀጣይ የኢኮኖሚ አሻጥር ለመከላከል ፣የመጋዘን ፍተሻ የነዳጅ ፣ የገቢ ስወራ በመከላከል ረገድም ትልቅ ለውጥ መምጣት መቻሉን ገልጸዋል።