በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ ላይ የክፍለ ከተሞች ከፍተኛ አመራሮች፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች እና የሰላም ሠራዊት አባላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ደረጀ እንደተናገሩት “በመትከል ማንሰራራት ” በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በአገር አቀፍ ደረጃ ችግኞችን እየተተከሉ ይገኛል ይህንን ግብ ለማሳካት የከተማዋ የሰላምና ጸጥታ አካላት የጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በዛሬው መርሐ ግብር ችግኞችን እንደሚተክሉ ገልጸዋል ።
የጸጥታ መዋቅሩ የአገርና የሕዝብን ሰላምና ደህንነት በማስጠበቅ የሰላም ዘብነቱን በተግባር ያረጋገጠ መሆኑን ገልጸው ፣ ከሰላም ማስጠበቅ ጎን ለጎን በአገር ልማት ላይ በንቃት እየተሳተፈ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
የሰላምና ጸጥታ አካላት ለሰላም መከበር ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ በተጨማሪ የአረንጓዴ አሻራ ግብ እንዲሳካ ላደረጉት ርብርብ ምስጋና አቅርበዋል።