Loading...

ዝርዝር ዜና

.የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት የጋሞ ሽማግሌዎች ባህላዊ የፍትህ ስርዓት ምርጥ ተሞክሮ ለማስፋት የተደረገ የዕርቅ ስነ ስርዓት፤

user 13-Jun-2025 ልማት

በቀን 6-09-2017 ዓ.ም በህብረተሰቡ ውስጥ የሚገኙ ባህላዊ የሆኑ እሴቶችን በመጠቀም ለሰላም እሴት ግንባታ ማዋል እንደሚገባ ተገለጸ።

‎የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት በክፍለ ከተማው ወረዳ 6 የሚገኘውን የጋሞ ሽማግሌዎች ባህላዊ የፍትህ ስርዓት ምርጥ ተሞክሮ ለማስፋት ያለመ ተግባር ተከናውኗል።

‎የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ደረጀ እንደተናገሩት በክፍለ ከተማችን የሚገኙ ህብረተሰቡ ለዘመናት ጠብቆ ያኖራቸው እሴቶች በመጠቀም የሰላም እሴት ግንባታ ስራዎቻችን ማዋል ይገባል ያሉ ሲሆን የጋሞ አባቶች የሽምግልና ስርዓት አንዱ ነው ብለዋል።

‎የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት የሰላም እሴት ግንባታ ስራዎች አስተባባሪ አቶ ፍቅሩ ጠና በበኩላቸው በክፍለ ከተማችን የሚገኘው የጋሞ አባቶች የዕርቅና የሽምግልና የዕርቅ ስርዓት ለሌሎች አካባቢዎች ተራደሽ መሆን ሚመገባና አስፍተን ልንበቀምበት የሚገባ ቱባ ባህላችን በመሆኑ ለማስፋት እንሰራለን ብለዋል።

‎በምልከታው ላይ የጋሞ ሽማግሌዎች የዕርቅ ስነ ስርዓት በማከናወን የዕርቅ ስነ ስርዓት ተካሄዷል ።