Loading...

ዝርዝር ዜና

.የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወራት ዕቅድ አፈጻጸሙን ከባለድርሻ አካላት ጋር የተደረገ ውይይት

user 13-Jun-2025 ልማት

በቀን 29 -08 -2017 ዓ.ም የሰላም ሰራዊቱ ከጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት የአካባቢያቸውን ሰላምና ጸጥታ ማስጠበቅ እንደሚገባ ተገለጸ።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወራት ዕቅድ አፈጻጸሙን ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድገዋል፡፡

ጽ/ቤቱ በበጀት ዓመቱ በባለፉት 9 ወራት አፈጻጸሙ በ10ሩም ወረዳ የሚገኙ የሰላም ሰራዊት የማነቃቃትና የመደገፍ ፣ ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት እንዲሆን የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መስራት ሃይማኖታዊና ህዝባዊ የሆኑ በዓላት በሰላም እንዲጠናቀቁ የተሰራበት ፣ የተለያዩ ህገ ወጥ ተግባራትና የደንብ ጥሰት ወንጀሎችን የመከላከል ፣ የጸረ ሰላም ሃይሎች እንቅስቃሴ በጋራ የመመከት ስራ መሰራቱን በቀረበው ሪፖርት ተገልጿል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ደረጀ እንደተናገሩት በበጀት ዓመቱ በባለፉት 9 ወራት በሰላምና ጸጥታ ግባችን ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት ማድረግ ሲሆን ለዚህም የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎትን በማስፋፋት ፣ የሰላም ሰራዊትን ማጠናከር እንዲሁም ከህዝብ ጋር ተቀናጅቶ በመስራት ህገ-ወጦችን መከላከል ፣ መቆጠጠርና በጋራ እርምጃ መዉሰድ ሲቻል መሆኑን ገልጸው ጽ/ቤቱ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የተሻለና ዉጤታማ ስራ መሰራት መቻሉን ተናግረዋል ፡፡