የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብሩን ያስጀመሩት የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንደተናገሩት በሰው ተኮር ስራዎች መንግስት የአቅመ ደካማ ቤቶችን በማደስ አብሮነትን መረዳዳትን ባህል ለማድረግ በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል።
ቢሮ ኃላፊዋ አክለውም የ13ኛ ዙር የብሔራዊ በጎ ፈቃድ ወጣቶች አብሮነት ለማሳደግ አንድነትን ለማጽናት ለሀገር ተረካቢ ወጣቶች አርዓ ያ በመሆን ለምትሰሩት ተግባር ልትመሰገኑ ይገባል ካሉ በኋላ በ11ዱም ክፍለ ከተማደረጃቸውን የጠበቁ ቤቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ ገንብተን እናስረክባለን ብለዋል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ በበኩላቸው በክፍለ ከተማው ሰው ተኮር የሆኑ በርካታ የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራት በመከናወን ላይ ይገኛል ያሉ ሲሆን በመረዳዳትና በመተጋገዝ ድህነትን እናሸንፋለን ያሉ ሲሆን አቅመ ደካሞችን ችግር በመረዳት ድጋፍ የሚያደርጉ ተቋማትና የግል ባለሀብቶች ሊመሰገኑ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
የከተማ ፣የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች ነዋሪዎች ብሔራዊ የበጎ ፈቃደኞች በተገኙበት የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳት ማስጀመር መርሃ-ግብር ተከናውኗል።