Loading...

ዝርዝር ዜና

.ጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት ለ7ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ የክረምት ችግኝ ተከላ ፕሮግራም የጉድጓድ ቁፋሮ መርሃ ግብር በእንጦጦ ፓርክ ሲካሄድ

user 13-Jun-2025 ልማት

በቀን 20 -09 - 2017 ዓ.ምየጸጥታ መዋቅሩ አባላት የህብረተሰቡን ሰላምና ጸጥታ ከማስከበር ባሻገር በአረንጓዴ አሻራ ላይ ተሳታፊ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

‎የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ለ7ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ የክረምት ችግኝ ተከላ ፕሮግራም የጉድጓድ ቁፋሮ መርሃ ግብር በእንጦጦ ፓርክ አካሄዷል፡፡

‎በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ታደሰ እንደተናገሩት በክፍለ ከተማው በባለፉት አመታት በተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር  በርካታ ችግኞች ተተክለው በአየር ንብረት ለውጥ ላይ አዎንታዊ ሚና በመጫወት ላይ ናቸው በዚህም ዓመት ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ችግኞች ሀገር በቀል ችግኞች የመተካት ስራ ይከናወናል ያሉ ሲሆን ለዚህ ቅድመ ዝግጅት የጉድጓድ ዝግጅት በተለያዩ አካላት እየተካሄደ ይገኛል ያሉ ሲሆን በዛሬው ዕለት የጸጥታ አካላት የከተማውን ሰላም ከማስጠበቅ ባለፈ ማህበራዊ ኃላፊነታችሁን ለመወጣት  በነቃ ተሳትፎ ላደረጉት አስተዋጽዖ በአስተዳደሩ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ደረጀ እንደገለጹት በክረምቱ መርሃ ግብር ለሚካሄደው የችግኝ ጉድጓድ ቁፋሮ  የፌደራልና የከተማ ፖሊስ አባላት  የተሳተፉ ሲሆን ፖሊሶች የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ከማረጋገጥ ባሻገር አረንጓዴ አሻራን በማኖር  ሀገራዊ ኃላፊነትን ለመወጣት እያደረጉ ያለው ተግባር በጥሩ ሞራልና ተነሳሽነት ጉድጓዶችን በመቆፈር ስራዎች  እያከናወኑ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

‎የክፍለ ከተማው ከተማ ፣ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ኤደን ካሳ በበኩላቸው በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ቅድመ ዝግጅት የጉድጓድ ቁፋሮ የጸጥታ አካላት እያደረጉ ላሉት አስተዋፅኦ ምስጋናቸውን ገልጸዋል።

‎በመርሃ ግብሩ ላይ የፌደራልና የከተማ ፖሊስ አባላት ፣ የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች ፣ የተለያዩ አካላት ተሳትፈውበታል።