Loading...

ዝርዝር ዜና

.ጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት በባለፉት 11ወራት በተሰሩ የሰላምና ጸጥታ ስራዎች እንዲሁም በወቅታዊ የሰላምና ጸጥታ ዙሪያ ከተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎችና ከባለድርሻ አካላት ጋር የተደረገ ዉይይት

user 13-Jun-2025 ፀጥታ

በቀን 21 -09 - 2017 ዓ.ም ህብረተሰቡና ባለድርሻ አካላት የክፍለ ከተማውን ሰላምና ጸጥታ በማስጠበቅ ላይ ከአስተዳደሩ ጋር በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው ተገለጸ።

‎‎

‎የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት በበጀት ዓመቱ በባለፉት 11ወራት በተሰሩ የሰላምና ጸጥታ ስራዎች እንዲሁም በወቅታዊ የሰላምና ጸጥታ ዙሪያ ከተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎችና ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል ፡፡

‎ ጽ/ቤቱ በባለፉት 11 ወራት በክፍለ ከተማው የተከናወኑና ወቅታዊ የሰላምና ጸጥታ ነባራዊ ሁኔታዎች የቀረቡ ሲሆን የሰላም ሰራዊቱ ያለበት ዝግጅት ናሁኔታ፣ በበክፍለ ከተማው ያሉ የስጋት ቦታዎችን በመለየት የስምሪት አግባቡን የማየት ፣ከትምህርት ቤቶች እና የሃይማኖት ተቋማት ደህንነታቸውን በማስጠበቅ ፣ ከሸገር አጎራባች ክፍለ ከተሞች ጋር የቅንጅት ስራዎችን መሰራታቸው ተገልጿል።

‎በውይይቱ ላይ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ደረጀ እንደተናገሩት አስተዳደሩ የክፍለ ከተማወን ሰላም እና ጸጥታ ለማስጠበቅ ህብረተሰቡ የሰላሙ ባለቤት እንዲሆን በተከናወነ ተግባር አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል የሰላም ሰራዊት ከሌሎች ጸጥታ አካላት ጋር በማቀናጀት የሰላም ሁኔታ በመቆጣጠር ህብረተሰቡ ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲኖር የማድረግ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸው ህብረተሰቡ የሰላም ስጋት የሆኑ ቦታዎችን መረጃ በመስጠት እና በመቀልበስ ለሰላም ተግቶ መስራት እንዳለበት ተናግረዋል ፡፡

‎ ኃላፊው አክለውም ፖሊስ ከሌሎች የጸጥታ መዋቅሮች ጋር በመቀናጀት የግል ፤ የሀይማኖት እና የመንግስት ተቋማትን የሰላም ሁኔታ በመጠበቅ አመርቂ የሰላም ሁኔታ እንዲፈጠር በትኩረት እየሰራ መሆኑን ተከትሎ የሰላም ሰራዊት የወንጀል መከላከል እና አጠባበቅ ግንዛቤአቸውን በማስፋት የህብረተሰቡን እና ሰላም በማስከበር ትልቅ ሚና ተወጠዋል ብለዋል የዚህ ውጤት ደሞ እዚህ ያለን ባለ ድርሻ አካላት ውጤት በመሆኑ በቀጣይም ቅንጅታችንን አጠናክረን መስራት አለብን ብለዋል።

‎የመድረኩ ተሳታፊዎችም እስካሁን የተሰራው ስራ የአስተዳደሩ ጥንካሬ ነው ህዝቡም የጸጥታ ባለቤት ሆኖ ለሰላም ተግቶ በመስራት አስተዳደሩን ማገዝ አለብን ብለዋል።

‎በመጨረሻም ከመድረኩ ተሳታፊዎች የተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ላይ ማብራሪያ በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል።