በቀን በቀን 01 -08 -2017 ዓ.ምበሰላም ጉዳይ የማህበረሰብ ተኮር ምክክር የጋራ ችግሮችን የሚፈቱበት መድረክ ነው ተባለ።
የጉለሌክፍለ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ለብሎክ ማህበረሰብ ተኮር ምክክር መድረክ አመቻቾች እና ለመድረኩ አስተባባሪዎች ፣ ለጽ/ቤት ኃላፊዎች ለተለያዩ ባለድርሻ አካላት የማህበረሰብ ተኮር ምክክር ማመቻቸትና ግጭት አፈታት እንዲሁም የተግባቦት ክህሎቶችን የሚያዳብር ስልጠና መስጠቱን አስታውቋል።
የመድረኩ ዓላማ ከቤተሰብና መንደር አንስቶ መላው ማህበረሰብ በየደረጃው በአካባቢያዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ስልጡን ምክክር በማድረግ የጋራ አረዳድ እና ብሔራዊ መግባባት የሚመጣበትን መንገድ ለማመቻቸት ያለመ እንደሆነ ተገልጿል።
ከብሔራዊ የማህበረሰብ ምክክሩ ከሚጠበቁ በርካታ ውጤቶች መካከል ስልጡን፣ ምክንያታዊና ሞጋች ማህበረሰባዊ መፍጠር ዋነኛው ነው ተብሏል፡፡
የአስተሳሰብ ልዕልና ያለው፣ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ስልጡን በሆነ መንገድ በራሱ የሚፈታ እና ቀጣይነት ያለው እድገት የሚያረጋግጥ ማህበረሰባዊ አቅም መፍጠር ነው ።
የማህበረሰብ ተኮር ምክክር ማመቻቸትና ግጭት አፈታት እንዲሁም የተግባቦት ክህሎቶችን በዝርዝር የግንዛቤ ማስጨበጫው ሲቀርብ ተሳታፊዎች ግንዛቤው በአብሮነት ለመኖርና ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ የየድርሻን እንድንወጣ ያግዛል ብለዋል።