በቀን 12-08-2017 ዓ.ም የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር መጪውን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ ለጸጥታ አካላት የቁም እንስሳት በስጦታ አበረከተ፡፡
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እንደተናገሩት የጸጥታ ሃይሉ የክፍለከተማውን ሰላምና ጸጥታ በማስጠበቅ ህብረተሰቡ በዓሉን በሰላም እንዲያከብር ሚናው የጎላ በመሆኑ አስተዳደሩ አጋርነቱን ለመግለጽ ድጋፍ አድርጓል ብለዋል፡፡
የክፍለ ከተማው ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ደረጀ በበኩላቸው በክፍለ ከተማው የሚገኙ የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ፣ለማዘዣ ጣቢያዎች ፣ ለፌዴራል ፖሊስ ፣ለደንብ ማስከበር ፣ለእሳት አደጋና ስጋት ቁጥጥር ፣ ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል