Loading...

ዝርዝር ዜና

‎የሰላምና ጸጥታ ስራዎቸ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ የመረጃ ልውውጥ ስርዓቱን በማጠናከር የሚፈጸሙ ወንጀሎችን መከላከል እንደሚገባ ተገለጸ። ‎

user 13-Jun-2025 ልማት

‎የሰላምና ጸጥታ ስራዎቸ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ የመረጃ ልውውጥ ስርዓቱን በማጠናከር የሚፈጸሙ ወንጀሎችን መከላከል እንደሚገባ ተገለጸ።

‎የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመረጃ መለዋወጫና ዌብሳይት የማስተዋወቅ እና የጋሞ ሽማግሌዎች ባህላዊ የፍትህ ስርዓት ምርጥ ተሞክሮ ለማስፋት ያለመ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር መድረክ ተካሄዷል።

‎የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ደረጀ እንደተናገሩት የሰላምና ጸጥታ ስራዎችን ከዘመኑ ጋር እየተቀያየሩ የሚመጡ በመሆኑ ዘመኑን የደረሰበትን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ወንጀሎችኖ መከላከልና የመረጃ ልውውጡን ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንዲሆን የዌብ ሳይት እንዲሁም ህብረተሰቡ መረጃዎችን የሚሰጥበት መተግበሪያ ክፍት አድርገናል ያሉ ሲሆን በክፍለ ከተማችን የሚገኙ ህብረተሰቡ ለዘመናት ጠብቆ ያኖራቸው እሴቶች በመጠቀም የሰላም እሴት ግንባታ ስራዎቻችን ማዋል ይገባል ያሉ ሲሆን የጋሞ አባቶች የሽምግልና ስርዓት አንዱ ነው ብለዋል።

‎በክፍለ ከተማችን የሚገኘው የጋሞ አባቶች የዕርቅና የሽምግልና የዕርቅ ስርዓት ለሌሎች አካባቢዎች ተራደሽ መሆን ሚመገባና አስፍተን ልንበቀምበት የሚገባ ቱባ ባህላችን በመሆኑ ለማስፋት እንሰራለን ብለዋል።